ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ከህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ከክቡር ሙራሊደሃራን ጋር በመሆን በኢትዮ-ሕንድ ቢዝነስ ፎረም ላይ ዛሬ የካቲት 10 ቀን 2013 ተሳትፈዋል፡፡.

+4
የኢትዮ-ህንድ ቢዝነስ ፎረም በኒውደልሂ ተካሄደ
======================
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ከህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ከክቡር ሙራሊደሃራን ጋር በመሆን በኢትዮ-ሕንድ ቢዝነስ ፎረም ላይ ዛሬ የካቲት 10 ቀን 2013 ተሳትፈዋል፡፡.
አቶ ደመቀ የህንድ ኩባንያዎች በአገራችን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ምንጭ በመሆን ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን አስታውሰው፤ በተለይም 30 የሕንድ ኩባንያዎች በአገራችን ወደ ሥራ በመግባት ላሳዩት ቁርጠኝነት አድንቆታቸውን ገልጸዋል፡፡
አገራችን ካላት ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ ፣ ከፍተኛ ቁጥርና ማሰልጠን የሚቻል የሰው ኃይል ፣ ተወዳዳሪ የኢኮኖሚ ማበረታቻዎችን ፣ ለባለሀብቶች በቂ ዋስትናዎችን እና ሙስናን ያለመቻቻል ፖሊሲ ታሳቢ በማድረግ ሌሎች ባለሀብቶችም ኢንቨስት እንዲያደርጉ አቶ ደመቀ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ለዚህም የአገሪቱ 10 ዓመት የኢኮኖሚ ልማት ዕቅድ በዲጅታል እንዲሁም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ትኩረት የሰጠ በመሆኑ ፤ የህንድ ባለሀብቶ እንዲሰማሩ ጠይቀዋል፡፡
ክቡር ሙራሌደሃን በበኩላቸው በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነት በማድነቅ የተናገሩ ሲሆን በህንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ግንኙነት በልዩ ልዩ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶች የበለጠ ማጠናከሩ አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል ፡፡በኢትዮጵያ ኢንቨስት እያደረጉ ያሉ አንዳንድ የህንድ ኩባንያዎች ተወካዮች እና አመራሮች በአገራችን ኢኮኖሚ መሳተፍ ያለውን ጥቅም አስረድተዋል ፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ በአሁኑ ወቅት በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ መጠን 1.3 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር መሆኑን ተገልጿል፡፡
0
People Reached
0
Engagements
Boost Unavailable
Like

 

Comment
Share
Posted in News.

Leave a Reply