ሰበር ዜና የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሌሎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ዋነኛ የጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ

+3
ሰበር ዜና
የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሌሎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ዋነኛ የጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ
**********************
የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱና ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አብርሃም ተከስተን ጨምሮ አገር ለመበታተን ሲሰሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት የሕወሃት ጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ።
የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ጥምር ሃይል አገር በመከላኪያ ሠራዊት ላይ ጥቃት በማድረስ አገር ለመበታተን ሲሰሩ የነበሩ የአሸባሪው ህወሃት አባላትን ለሕግ የማቅረብ ተልዕኮ እንደቀጠለ ነው።
በምሥራቅ ዕዝ 28ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ብርጌድ ኃይል አዛዥ መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ፣ ሠራዊቱ እነዚህን ተፈላጊዎች በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ አልፎ አስሶ እንዳገኛቸው ተናግረዋል።
እነዚህን ተፈላጊዎች ለመያዝ የሕዝቡ ድጋፍ ለመከላከያ ሠራዊት ኃይል እንደሆነው የገለጹት አዛዡ፣ በቀጣይም የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገውን መረጃ እንዲያገኝ ለማድረግ ተግቶ አየሠራ መሆኑንም አክለዋል።
በጥላሁን ካሣ
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
በምስል የሚገኙ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የኢንስታግራም ገፃችንን ይከተሉ
አጫጭርና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
Posted in News.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *