ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤታችን በአገራችን የተከሰተውን የCOVID-19ን ለመከላከል የሚረዳ የግማሽ ሚሊየን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎችን ከTechnical University of Munich ድጋፍ አገኘ፤

ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤታችን በአገራችን የተከሰተውን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚረዳ የግማሽ ሚሊየን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎችን ከTechnical University of Munich ሴፕቴምበር 10 ቀን 2020 በባቫሪያ ፌዴራል ግዛት ዋና ከተማ በሆነቸው ሙኒክ በመገኘት ድጋፉን ተረክቧል።
በስነ ስረዓቱ ላይ የቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት ተወካይ የሆኑት አምባሳደር በረደድ አንሙት እና የቢዚነስ ዲፕሎማሲ ዘርፍ ጉዳዮች ክፍል ኃላፊ ወ/ሮ ኡባህ መሀመድ የተገኙ ሲሆን፣ አገራችን በሽታውን ለመቆጣጠር እያደረገች ያለችውን ጥረት በማስረዳት ፣ በአገራችን እየተደረገ ያሉ ሁለንትናዊ ተጨባጭ ለውጦች ዙርያ ላይ ሰፊ ገለጻ ሰጥተዋል። እንዲሁም ተቋሙ በሽታውን ለመከላከል ለአገራችን ላበረከተው ድጋፍ እውቅና በመስጠት በጽ/ቤታችን በኩል የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።
በዩንቨርሲቲው በኩል የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት Prof. Dr. Juliane Winkelmann ተቋሙ በህክምና ዘርፍ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦና ስራዎች ላይ ሰፊ ገላጻ ያደረጉ ሲሆን፣ የመስክ ጉብኝትም ተደርጓል።
ከዚህ በተጨማሪ ተቋሙ በአፍሪካ ለግብርናው ዘርፍ ጠቃሚ የሆነ የኤሌክትሪክ መኪና አምርቶ በቅርቡ ተቀባይነት ማግኘቱን በዚሁ ወቅት ገለጻ የተደረገ ሲሆን፣ በአገራችንም በዚሁ ረገድ ጥናቶች መጀመራቸውንና በቅርቡ በ2022 ተግባራዊ ሙከራ እንደሚያደርጉ ለመረዳት ተችሏል።
1,758
People Reached
178
Engagements
Boost Post
18
5 Shares
Like

Comment
Share
Posted in News.

Leave a Reply