በትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ የሚሰጡ ዓለም አቀፍ ረጅ ተቋማት በማሳወቅ ብቻ እየገቡ ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

5h 
በትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ የሚሰጡ ዓለም አቀፍ ረጅ ተቋማት በማሳወቅ ብቻ እየገቡ ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዚህ ቀደም በፍቃድ ይገቡ የነበሩ በትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ የሚሰጡ ዓለም አቀፍ ረጅ ተቋማት አሁን ላይ በማሳወቅ ብቻ እየገቡ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህም በትግራይ ክልል የሚነሳውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በተመለከተ የማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ የህግ ጥሰት ፈፅመዋል የተባሉ አካላትን ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ ስለመሆኑም ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በክልሉ ከሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ጋር ተያይዞ መንግስት 70 በመቶውን ማቅረቡን አስረድተዋል።
ከሰብአዊ መብት ጋር በተያያዘም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 46ኛው የሰብአዊ ቶች ጉባኤ ኢትዮጵያ በሰብአዊ መብት ጉዳይ ላይ የበኩሏን እንደምትወጣ እና ለዚህም ቁርጠኛ ስለመሆኗ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኩል ገለጻ መደረጉንም አውስተዋል፡፡
በይስማው አደራው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Posted in News.

Leave a Reply