በኢትዮጵያ ተጨማሪ 141 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፣ በበሽታው የ3 ሰዎች ሕይወትም አለፈ፣

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 141 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፣ በበሽታው የ3 ሰዎች ሕይወትም አለፈ
**********************************************

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4675 የላቦራቶሪ ምርመራ 141 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
በአጠቃላይ በአገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5175 ደርሷል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ከ2 ወር እስከ 87 ዓመት የዕድሜ ክልል የሚገኙ 81 ወንድ እና 60 ሴት መሆናቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዜግነት 139 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ሁለት ሰዎች የውጭ ዜጋ መሆናቸው ተገልጿል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች በቦታ ሲለዩ፣

* 113 ሰዎች ከአዲስ አበባ
* 15 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል
* 6 ሰዎች ከሐረሪ ክልል
* 3 ሰዎች ከጋምቤላ ክልል
* 2 ሰዎች ከሶማሊ ክልል
* 1 ሰው ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር
* 1 ሰው ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ናቸው።

ተጨማሪ 58 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገሪቱ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1544 ደርሷል፡፡

በበሽታው የተጨማሪ 3 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገሪቱ በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 81 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ገጻችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW

Image may contain: 1 person
Image may contain: text
Posted in News.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *