በኢትዮጵያ ተጨማሪ 46 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

 

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3410 የላቦራቶሪ ምርመራ 46 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 701 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በተጓዳኝ ሕመም ምክንያት በጽኑ ሕክምና ላይ የነበረችና በትናንትና እለት የኮሮና ቫይረስ በምርመራ የተገኘባት የ32 ዓመት የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነች ኢትዮጵያዊት ትናንት ሌሊት ሕይወቷ አልፏል፡፡ በዚህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 6 ደርሷል፡፡

ተጨማሪ 8 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገሪቱ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 167 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 29 ወንድ እና 17 ሴቶች ሲሆኑ ናቸው። በዜግነት 45 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንዷ የእስራኤል ዜጋ ናት። ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከ12 እስከ 79 ዓመት መሆኑ ተገልጿል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 13 ሰዎች ከአዲስ አበባ (4ቱ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው፣ አንድ ሰው የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው እና 8 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋርም በግልጽ የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው ናቸው)፣ 3 ሰዎች ከትግራይ ክልል (ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው እና በለይቶ ማቆያ ያሉ)፣ 15 ሰዎች ከአማራ ክልል (ሁሉም የውጭ አገራት የጉዞ ታሪክ ያላቸውና በላይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ)፣ 11 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዙ ታሪክ ያላቸው እና ለይቶ ማቆያ ያሉ) እንዲሁም 4 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው የድንበር ተሻጋሪ መኪና አሽከርካሪዎች መሆናቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

እስካሁን በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሕክምና ላይ ያሉ ሰዎች ቁጥር 526 ሲሆን አንድ ሰው በፅኑ ሕክምና ላይ ይገኛል።

በኢትዮጵያ እስካሁን በአጠቃላይ 87 ሺህ 264 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

Image may contain: 1 person
Image may contain: text
No photo description available.
Posted in News.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *