በዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር የቫተር እስቴትን እህትማማቾች ጀርመን በሲድ ፕሮጀክት ትብብር ለስራ አጥ ወጣቶች ሰባት የልብስ ስፊት ማሽኖችና አንድ የኤለክትሪክ ዲናሞ ድጋፍ አደረገ ፡፡

በዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር የቫተር እስቴትን እህትማማቾች ጀርመን በሲድ ፕሮጀክት ትብብር ለስራ አጥ ወጣቶች ሰባት የልብስ ስፊት ማሽኖችና አንድ የኤለክትሪክ ዲናሞ ድጋፍ አደረገ ፡፡
የዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር የቫተር እስቴትን እህትማማቾች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ደሳለኝ ወንድምነህ በሰጡት መረጃ በሲድ ፕሮጀክት በኩል ከዚህ በፊት በርካታ ድጋፎች ሲደረጉ መቆየታቸውን ገልፀው አሁንም በድጋሜ በርካታ የከተማ ስራ አጥ ወጣቶች የማሰልጠኛና የስራ እድል መፍጠሪያ የሚሆኑ የልብስ ስፌት ማሽኖችን በስምንት መቶ ሀምሳ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር (853.920.22 ወጭ በማድረግ ገዝተው ለከተማ አስተዳደሩ በድጋፍ አበርክተዋል፡፡
በዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር ዋነ ከንቲባ አቶ ጌቱ ቅጣው ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ቸረው ለቀጣይ በርካታ የከተማዋ ተወላጅ የስራ አጥ ወጣቶች የስልጠና ፕሮግራምና የስራ እድል ፈጠራን አንድ እርምጃ ሚያጉዝ እንደሆነ ገልፀው የአካባቢያችንን ባህልና ወግ ለአለም የማሳወቅና የማዘመን ስራ እንደሚሰራም አስረድተዋል፡፡
በመጨረሻም ወጣቱ በዚህ ስልጠና ላይ ተሳታፊ በመሆን የራሱን ህይወት በመቀየር ለሀገርና ለወገኑ ጠቃሚ እንዲሆን ጭምር መደላድል ይፈጥራልም ብለዋል ፡፡
Posted in News.

Leave a Reply