ባለፉት 4 ወራት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ከ190 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

ባለፉት 4 ወራት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ከ190 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ
*****************************************
ባለፉት አራት ወራት ለታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ190 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የግድብ ህዝባዊ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
በዚህም ህብረተሰቡ ለግድቡ ግንባታ የሚያደረገውን ድጋፍና አስተዋጽኦ አጠናክሮ መቀጠሉን የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኘኑት ኃላፊ አቶ ኃይሉ አብረሃም ተናግረዋል፡፡
ግድቡን ለማገባደድ የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ረገድ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን አስረድተዋል።
ለዚህም የ8100 ተሳትፎ አንዱ ማሳያ ነው ያሉት ኃላፊው፤ የሰኔ ወር ሪፖርትን ሳይጨምር ከ8100፣ ከቦንድና ከስጦታ 668 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አመልክተዋል።
የኮሮናቫይረስ በሀገራችን ከተከሰተ ወዲህ ብቻ ከ190 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡንም አቶ ኃይሉ አስታውቀዋል።
ምክር ቤቱ የቫይረሱ ስርጭት ያስከተለው ክልከላ ባቀደው ልክ ለመንቀሳቀስ እንዳላስቻለውም ጠቁሟል።
ይሁን እንጂ ህብረተሰቡ በ8100 ላይ በመሳተፍ፣ ቦንድ በመግዛትና ስጦታ በመስጠት ግድቡን በመደገፍ ላይ እንደሚገኝ ኃላፊው ተናግረዋል።
በቀጣይም የህብረተሰቡን ተሳትፎ የሚያሳድጉና ግንዛቤውን የሚያጎለብቱ ሥራዎች በሚዲያ ላይ እንደሚሠሩም ምክር ቤቱ ማሳወቁን ኢዜአ ዘግቧል።
Image may contain: sky and outdoor
Amen Amen, Efi Jacob and 1.3K others
173 Comments
46 Shares
Like

Comment

Share

Posted in News.

2 Comments

  1. Good day! Would you mind if I share your blog with my facebook group? There’s a lot of folks that I think would really appreciate your content. Please let me know. Thank you

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *