ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን ልዩነታቸውን በውይይት እንዲፈቱ የአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ፤

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘ ያላቸውን ልዩነት በውይይት እንዲፈቱ የአፍሪካ ህብረት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት ገልጸዋል።

ሙሳ ፋኪ ማህመት ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም አቶ ገዱ ኢትየጵያ፣ ግብጽና ሱዳን ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘ እስከዛሬ ድረስ የደረጓቸውን ውይይቶች እና የኢትዮጵያን አቋም በተመለከተ ገለጻ አድርገውላቸዋል።

አቶ ገዱ ከአባይ ውሀ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ባልተሳተፈችባቸው የተፈረሙትን የቅኝ ግዛት ውሎች እንደማትቀበልም በዚህ ወቅት ገልጸዋል።

የግድቡን የመጀመሪያ ዙር የውሀ ሙሌት በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ለማከናወን አስፈላጊው ስራ እየተከናወነ መሆኑንም አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብቷን በመጠቀም ልማቷን የማፋጠን ህጋዊ እና ተፈጥሯዊ መብቷ መሆኑን በማስታወስም የአፍሪካ ህብረት በመርህ ለይ የተመሰረተ ድጋፉን ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት በበኩላቸው ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች እንደሚያስፈልጋቸው እንደሚያምኑ አንስተዋል።

የአፍሪካ ህብረት በዚህ በኩል ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት የጋኘነው መረጃ ያመላክታል።

ህብረቱ ሶስቱ ሃገራት ተቀራርበው ልዩነታቸውን በውይይት እንዲፈቱ የውይይት መድረኮችን ለማመቻቸት እንደሚንቀሳቀስም በዚህ ወቅት ጠቁመዋል።

Image may contain: 2 people, people standing
Posted in News.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *