ክቡር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከፖርቱጋል አቻቸው ቴሬዛ ሪቤይሮ ጋር ተወያዩ

===================================
የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከፖርቱጋል አቻቸው ክብርት ቴሬዛ ሪቤይሮ ጋር ዛሬ መስከረም 4 ቀን 2013 ዓም በዙም የሁለቱን አገራት ግንኙነት ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
ክቡር አምበሳደር ሬድዋን ሁሴን የሁለቱ አገራት ግንኙነት ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ መሆኑን በማስታውስ፤ ፖርቱጋል የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆና በመመረጧ ደስታቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ፖርቱጋል የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በመሆን በምትቆይበት ወቅት ከዚህ ቀደም የነበሩ የሁለትዮሽና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር መስራቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል አምባሳደር ሬድዋን አንስተዋል።
የአውሮፓ ህብረት እና የአፍሪካ ህብረት ባላቸው ጠንካራ ትብብር የስደተኞችን ጉዳይ እልባት ለመስጠት ጥረታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እምነታቸው መሆኑንም አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገልጸዋል።
ሁለቱ አህጉሮች የህዝቦቻቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚ ልማት፣ በኢንስትመንት እና በንግድ ግንኙነታቸውን አሁን ካለበት ይበልጥ ማጠናከር እንዳለባቸውም አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አሳስበዋል።
ክብርት ቴሬዛ ሪቤይሮ በበኩላቸው የኢትዮጵያ 2013 አዲስ ዓመት ለህዝቦቿ የስኬት ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ፖርቱጋል ከኢትዮጵያ እና ከአፍሪካ ጋር ላላት ግንኙነት ልዩ ትርጉም እንደምትሰጥም ክብርት ቴሬዛ ሪቤይሮ በዚህ ወቅት ገልጸዋል።
ፓርቱጋል በአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ዘመኗ ከአፍሪካ ጋር በትብብር ለመስራት ቅድሚያ እንደምትሰጥ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያና ፖርቱጋል የፖለቲካ ምክክርን ጨምሮ ሌሎች መድረኮችን በስፋት በመጠቀም ትብብራቸውን ይበልጥ ማስፋት እንደሚጠበቅባቸውም ቴሬዛ ሪቤይሮ አሳስበዋል።
ሁለቱ አገራት የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በበጋራ ለመከላከልም በትብብር መስራታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ክብርት ቴሬዛ ሪቤይሮ በዚህ ወቅት አረጋግጠዋል።
Posted in News.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *