የቆንስላ አገልግሎት

በቆንስላ ክፍል የሚሰጡ ዋናዋና አገልግሎቶች ዝርዝር፣ የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች፣የአፈጻጸም ደረጃና መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

1. በውጭ የሚኖሩ ሰነድ አልባ ኢትዮዽያውያኖች ኢትዮጵየዊነታቸው እንደረጋገጥ የሚከተለውን ሰነዶች ይዘውና በአካል መጥተው ማመልከት አለባቸው 

 • የሰነድ አልባ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ መጠየቂያ ቅፅ 01 ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
  መጠየቂያ ቅፅ 03 ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
 • ከሚኖሩበት ሀገር የተሰጠ መኖርያ ፈቃድና የጉዞ ሰነድ አንድ ኮፒ ወይም ከሚኖሩበት ሀገር የተሰጠ ጊዜያዊ መታወቂያ አንድ ኮፒ
 • ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፎች ማቅረብ (ከጀርባው ሙሉ ስም የተፃፈበት፣ ከበስተኃላው ነጭ የሆነ፣ ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
 • የሚገኙበት ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ መፃፍ
 • አሻራ መስጠት
2.  አዲስ ፓስፖርት ለመጠየቅ
 • የፓስፖርት መጠየቂያ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
 • ከዚህ በፊት አሻራ ካልሰጡ በቆንስላ ፅ/ቤት በመገኘት አሻራ መስጠት
  የአሻራ መውሰጃ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
 • ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፎች ማቅረብ (ከጀርባው ሙሉ ስም የተፃፈበት፣ ከበስተኃላው ነጭ የሆነ፣ ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
 • ከኢትዮጵያ ሲወጡ የነበረው የኢትዮጵያ የቀድሞው አሻራ ስጥተው ያወጡት ፓስፖርት አንድ ኮፒ ማቅረብ
 •  የቀድሞው ፓስፖርት ኮፒ ከሌለ በሰነድ አልባ አመልክቶ ኢትዮጵያዊነት መጣራት አለበት
 • ከሚኖሩበት ሀገር የተሰጠ መኖርያ ፈቃድና የጉዞ ሰነድ አንድ ኮፒ ወይም ከሚኖሩበት ሀገር የተሰጠ ጊዜያዊ መታወቂያ አንድ ኮፒ
 • የስም ወይም የዕድሜ ለውጥ ካለ ከሚመለከተው ክፍል የተዘጋጀና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ማስረጃ አርጂናልና አንድ ኮፒ
 • አሻራ ካልሰጡ በአካል መገኘት ያስፈልጋል
 • የሚገኙበት ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ መፃፍ
 • ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 26 ደቂቃ
 • የአገልግሎት ክፍያ 54 €
 • አዲሱ ፓስፖርት ተሰርቶ እስኪመጣ ከሁለት እስከ ሶስት ወር ይቆያል
 • አዲሱ ፓስፖርት ከኢሚግሬሽን ተስርቶ ሲመጣ በፖስታ እንዲላክሎት መመለሻ ፖስታ ቴምብር (የ 4,05 €) ለጥፈውና አድራሻዎትን ፅፈው ይላኩልን
3.  ፓስፖርት ለማስቀየር (ለማሳደስ)
 • የፓስፖርት መጠየቂያ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
 • አገልግሎቱ ያበቃ ፓስፖርት ኦርጅናልና  አንድ ኮፒ ማቅረብ
 • የጀርመን መኖሪያ ፈቃድ አንድ ኮፒ ማቅረብ
 • ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፎች ማቅረብ (ከጀርባው ሙሉ ስም የተፃፈበት፣ ከበስተኃላው ነጭ የሆነ፣ ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
 • ያለቀውን ፓስፖርት ሲያወጡ አሻራ ሰጥተው ከነበረ ሰነዶችን በፖስታ መላክ ይችላሉ በፖስታ ሲልኩ ፓስፖርት ኦርጂናልና የጀርመን መኖሪያ ፈቃድ አንድ ኮፒ ይላኩልን
 • አገልግሎቱ ያበቃው ፓስፖርት ሲወስዱ 14 ዓመት በታች ከነበሩ የግድ በአካል መምጣት ያስፈልጋል
 • የአገልግሎት ክፍያ 54 €
 • የስም ለውጥ ካለ ስም የለወጡብት ማስረጃ ማቅረብ
 • የስም ለውጥ ማስረጃው ከኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መረጋገጥ አለበት
 • የስም ለውጥ ማስረጃው ከጀርመን ከሆነ (ወደ አማርኛ ወይም ወደ እንግሊዝ ቋንቋ የተተረጎመ) እና በ Landgericht የተረጋገጠ አርጂናልና አንድ ኮፒ
 • የጀርመን አገር የስም ለውጥ ማስረጃ በቆንስላ ጽ/ቤት መረጋገጥ አለበት
 • ለስም ለውጥ ማስረጃ በቆንስላ ጽ/ቤት ለማረጋገጥ የአገልግሎት ክፍያ 53,10 € ነው
 • ሰነዶችን በፖስታ የሚልኩት ከሆነ ለአገልግሎት የሚከፈለው በአካውንታችን አስተላልፈውልን የከፈሉበት ማስረጃ (Kontoauszug) አብረው ይላኩልን
 • የሚገኙበት ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ መፃፍ
 • ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 26 ደቂቃ
 • አዲሱ ፓስፖርት ተሰርቶ እስኪመጣ ከሁለት እስከ ሶስት ወር ይቆያል
 • አዲሱ ፓስፖርት ከኢሚግሬሽን ተስርቶ ሲመጣ በፖስታ እንዲላክሎት መመለሻ ፖስታ ቴምብር (የ 4,05 €) ለጥፈውና አድራሻዎትን ፅፈው ይላኩልን:: በተጨማሪም አገልግሎቱ ያበቃው ፓስፖርት ይላኩልን
4.  በጠፋ ፓስፖርት ምትክ አዲስ ፓስፖርት ለመጠየቅ
 • የፓስፖርት መጠየቂያ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
 • ስለመጥፋቱ የፖሊስ ማስረጃ
 • የጠፋው ፓስፖርት አንድ  ኮፒ ማቅረብ
 • የጀርመን መኖሪያ ፈቃድ አንድ ኮፒ
 • ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፎች ማቅረብ (ከጀርባው ሙሉ ስም የተፃፈበት፣ ከበስተኃላው ነጭ የሆነ፣ ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
 • ለመጀመርያ ጊዜ በጠፋ ፓስፖርት ምትክ በመደበኛ ክፍያ ተጨማሪ 50% የአገልግሎት ክፍያ 81 €
 • ለሁለተኛ ጊዜ በጠፋ ፓስፖርት ምትክ በመደበኛ ክፍያ ተጨማሪ 100% የአገልግሎት ክፍያ 108 €
 • ለሶስተኛ ጊዜ በጠፋ ፓስፖርት ምትክ በአምስት ዓመት ውስጥ ጥያቄ ካቀረበ በመደበኛ ክፍያ ተጨማሪ 200% የአገልግሎት ክፍያ 162€
 • ሰነዶችን በፖስታ የሚልኩት ከሆነ ለአገልግሎት የሚከፈለው በአካውንታችን አስተላልፈውልን የከፈሉበት ማስረጃ (Kontoauszug) አብረው ይላኩልን
 • የሚገኙበት ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ መፃፍ
 • ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 26 ደቂቃ
 • አዲሱ ፓስፖርት ተሰርቶ እስኪመጣ ከሁለት እስከ ሶስት ወር ይቆያል
 • አዲሱ ፓስፖርት ከኢሚግሬሽን ተስርቶ ሲመጣ በፖስታ እንዲላክሎት መመለሻ ፖስታ ቴምብር (የ 4,05 €) ለጥፈውና አድራሻዎትን ፅፈው ይላኩልን
5.  አዲስ ፓስፖርት ለህጻን ልጅ ለማመልከት
 • የፓስፖርት መጠየቂያ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
 • ህፃኑ / ህፃኗ ፓስፖርት እንዲሰጠው  እንዲሰጣት የአባትና የእናት ስምምነት ያለበት ማመልከቻ ማቅረብ
 • የህፃኑ/የህፃኗ ሕጋዊ የልደት ምስክር ወረቀት (ወደ አማርኛ ወይም ወደ እንግሊዝ ቋንቋ የተተረጎመ) እና በ Landgericht የተረጋገጠ አርጂናልና አንድ ኮፒ
 • የተረጋገጠው የልደት ሰረቲፊኬት በቆንስላ ጽ/ቤትም ይረጋገጣል
 • የህፃኑ /የህፃኗ ሁለት  የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፎች ማቅረብ (ከጀርባው ሙሉ ስም የተፃፈበት፣ ከበስተኃላው ነጭ የሆነ፣ ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
 • ህፃኑ /ህፃኗ የሌላ ሀገር ዜግነት የሌለው / የሌላት መሆኑ / መሆኗ የሚያረጋግጥ ሰነድ አርጂናልና አንድ ኮፒ
 • የወላጆች ፓስፖርትና የጀርመን መኖሪድ ፈቃድ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ
 • የሚገኙበት ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ መፃፍ
 • ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 26 ደቂቃ
 • ለፓስፖርቱ የአገልግሎት ክፍያ 54 € ነው
 • የህፃኑ/የህፃኗ ሕጋዊ የልደት ምስክር ወረቀት በቆንስላ ጽ/ቤት ሲረጋገጥ የአገልግሎት ክፍያ 53.10 € ነው
 • ሰነዶችን በፖስታ የሚልኩት ከሆነ ለአገልግሎት የሚከፈለው በአካውንታችን አስተላልፈውልን የከፈሉበት ማስረጃ (Kontoauszug) አብረው ይላኩልን
 • አዲሱ ፓስፖርት ተሰርቶ እስኪመጣ ከሁለት እስከ ሶስት ወር ይቆያል
 • አዲሱ ፓስፖርት ከኢሚግሬሽን ተስርቶ ሲመጣ በፖስታ እንዲላክሎት መመለሻ ፖስታ ቴምብር (የ 4,05 €) ለጥፈውና አድራሻዎትን ፅፈው ይላኩልን በተጨማሪም ፖስታ ሲልኩ የልጅዎትን ስም ጠቅሰውና የልጅዎት ፓስፖርት እንዲላክሎት ማስታወሻ ይፃፉ
6.  አዲስ በትውልደ ኢትዮጵያዊ  የውጭ ዜጋ መታወቂያ ለማውጣትና ቢጫው መታወቂያ ለማስቀየር (ለማሳደስ)
 • ማመልከቻ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
 • የአመልካቹ አገልግሎቱ ቢያንስ 6 ወር የፀና ዜግነት ከተሠጠው አገር የተሰጠ ፓስፖርት አርጂናልና አንድ  ኮፒ
 • በትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ከነበርዎት ያለቀው በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ
 • የአመልካቹ ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፎች (ከጀርባው ሙሉ ስም የተፃፈበት፣ ከበስተኃላው ነጭ የሆነ፣ ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
 • የአመልካቹ አሻራ ተወስዶ የተሰጠ የኢትዮጵያ ፓስፖርት አንድ ኮፒ፤ ወይም
 • የአመልካቹ ያለአሻራ (አሻራ ሳይወሰድ) የተሰጠ የኢትዮጵያ ፓስፖርት አንድ ኮፒ እና አግባብ ባለው አካል የተሰጠና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የልደት ሰርተፊኬት አርጂናልና አንድ ኮፒ፤ ወይም
 • ከፍርድቤት የተሰጠ ሆኖ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የወላጅ የወራሽነት ማስረጃ አርጂናልና ከፍርድቤት የተሰጠ ሆኖ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የወላጅ የወራሽነት ማስረጃ ከፍርድቤት የተሰጠ ሆኖ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የወላጅ የወራሽነት ማስረጃ አንድ ኮፒ ወይም አንድ ኮፒ ወይም
 • ስልጣን ካለው ፍርድ ቤት የተሰጠና በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ  የኢትዮጵያዊ ልጅ የነበረ መሆኑና ለጉዲፈቻነት የተሰጠ እንደነበረ የሚያሳይ የወላጆች ማስረጃ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ ከሆነ በራሱ ጠያቂነት፣ ዕድሜው ከ18 በታች ከሆነም በአሳዳጊዎቹ ጠያቂነት፤ ወይም
 • ወላጆቹ ኢትዮጵያዊ ሆነው ስልጣን ካለው ፍርድ ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል ተረጋግጦ የቀረበ የአባትነት ወይም የእናትነት ማረጋገጫ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ፤ ወይም
 • በትውልድ ኢትዮጵያዊ ስለመሆንዎ የሚያሳይ ያሎትን ማስረጃ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ
 • አመልካቹ ውጭ አገር የተወለደ ከሆነ የአመልካቹ ሕጋዊ የልደት ምስክር ወረቀት (ወደ አማርኛ ወይም ወደ እንግሊዝ ቋንቋ የተተረጎመ) እና በ Landgericht የተረጋገጠ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ
 • በ Landgericht የተረጋገጠ የልደት ሰረቲፊኬት በቆንስላ ጽ/ቤትም ይረጋገጣል :: የልደት ሰርቲፊኬቱን ለማረጋገጥ የአገልግሎት ክፍያ 81 €
 • የስም ለውጥ ካለ የስም ለውጥ ያደረጉበት ማስረጃ ሰነድ (ወደ አማርኛ ወይም ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ የተተረጎመ) እና በ Landgericht ወይም በ ወይም በ የተረጋገጠ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ
 • የስም ለውጥ ያደረጉበት ማስረጃ ሰነድ በቆንስላ ጽ/ቤትም ይረጋገጣል:: ሰነዱን ለማረጋገጥ የአገልግሎት ክፍያ 81 € ነው
 • ለመታወቂያው የአገልግሎት ክፍያ የ200 (የአሜሪካን ዶላር) ተመጣጣኙን በቀኑ ምንዛሪ በዩሮ (€) ነው የሚከፈለው
 • የሚገኙበት ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ መፃፍ
 • ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 28 ደቂቃ
 • አዲሱ መታወቂያ ተሰርቶ እስኪመጣ ከሁለት እስከ ሶስት ወር ይቆያል
 • አዲሱ በትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ ከኢሚግሬሽን ተስርቶ ሲመጣ በፖስታ እንዲላክሎት መመለሻ ፖስታ ቴምብር (የ 4,05 €) ለጥፈውና አድራሻዎትን ፅፈው ይላኩልን:: በተጨማሪም አገልግሎቱ ያበቃው በትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ ይላኩልን
7.  አሻራ ተወስዶ የተሰጠ በትውልደ ኢትዮጵያዊ  የውጭ ዜጋ መታወቂያ ለማስቀየር (ለማሳደስ)
 • ማመልከቻ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
 • የአመልካቹ አገልግሎቱ ቢያንስ 6 ወር የፀና ዜግነት ከተሠጠው አገር የተሰጠ ፓስፖርት አርጅናልና አንድ  ኮፒ
 • ያለቀው በትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ
 • የአመልካቹ ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፎች (ከጀርባው ሙሉ ስም የተፃፈበት፣ ከበስተኃላው ነጭ የሆነ፣ ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
 • የስም ለውጥ ካለ የስም ለውጥ ያደረጉበት ማስረጃ ሰነድ (ወደ አማርኛ ወይም ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ የተተረጎመ) እና በ Landgericht የተረጋገጠ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ
 • የስም ለውጥ ያደረጉበት ማስረጃ ሰነድ በቆንስላ ጽ/ቤትም ይረጋገጣል:: ሰነዱን ለማረጋገጥ የአገልግሎት ክፍያ 81 € ነው 
 • ለመታወቂያው የአገልግሎት ክፍያ የ200 ለመታወቂያው (የአሜሪካን ዶላር) ተመጣጣኙን በቀኑ ምንዛሪ በዩሮ (€) ነው የሚከፈለው
 • የሚገኙበት ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ መፃፍ
 • ሰነዶችን በፖስታ የሚልኩት ከሆነ ለአገልግሎት የሚከፈለው በአካውንታችን አስተላልፈውልን የከፈሉበት ማስረጃ (Kontoauszug) አብረው ይላኩልን
 • ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 28 ደቂቃ
 • አዲሱ መታወቂያ ተሰርቶ እስኪመጣ ከሁለት እስከ ሶስት ወር ይቆያል
 • አዲሱ በትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ ከኢሚግሬሽን ተስርቶ ሲመጣ በፖስታ እንዲላክሎት መመለሻ ፖስታ ቴምብር (የ 4,05 €) ለጥፈውና አድራሻዎትን ፅፈው ይላኩልን:: በተጨማሪም አገልግሎቱ ያበቃው በትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ ይላኩልን
8. አካለ መጠን ላልደረሱ በውጭ ለተወለዱ የውጭ ዜጋ ለሆኑ የኢትዮጵያዊ ልጀችና በትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ ልጆች በትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ ለማመልከት
 • ማመልከቻ ቅፅ መሙላት መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
 • የልጁ አገልግሎቱ ቢያንስ ስድስት ወር የፀና ዜግነት ከተሠጠው አገር የተሰጠ ፓስፖርት ኦርጂናልና አንድ  ኮፒ
 • የልጁ ሕጋዊ የልደት ምስክር ወረቀት (ወደ አማርኛ ወይም ወደ እንግሊዝ ቋንቋ የተተረጎመ) እና በ Landgericht ወይም በ ወይም በ የተረጋገጠ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ
 • የተረጋገጠው የልደት ሰረቲፊኬት በቆንስላ ጽ/ቤትም ይረጋገጣል
 • የልጁ  ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፎች ማቅረብ (ከጀርባው ሙሉ ስም የተፃፈበት፣ ከበስተኃላው ነጭ የሆነ፣ ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
 • የወላጅ በትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ እና የጀርመን ፓሰፖርት
 • የልደት ሰርቲፊኬቱን ለማረጋገጥ የአገልግሎት ክፍያ 81 €
 • ለመታወቂያው የአገልግሎት ክፍያ የ20( የአሜሪካን ዶላር) ተመጣጣኙን በቀኑ ምንዛሪ በዩሮ (€) ነው የሚከፈለው
 • ሰነዶችን በፖስታ የሚልኩት ከሆነ ለአገልግሎት የሚከፈለው በአካውንታችን አስተላልፈውልን የከፈሉበት ማስረጃ (Kontoauszug) አብረው ይላኩልን
 • የሚገኙበት ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ መፃፍ
 • ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 28 ደቂቃ
 • አዲሱ መታወቂያ ተሰርቶ እስኪመጣ ከሁለት እስከ ሶስት ወር ይቆያል
 • አዲሱ በትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ ከኢሚግሬሽን ተስርቶ ሲመጣ በፖስታ እንዲላክሎት መመለሻ ፖስታ ቴምብር (የ 4,05 €) ለጥፈውና አድራሻዎትን ፅፈው ይላኩልን በተጨማሪም ፖስታ ሲልኩ የልጅዎትን ስም ጠቅሰውና የልጅዎት በትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ እንዲላክሎት ማስታወሻ ይፃፉ
9. በጋብቻ ወይም ለትዳር ጋደኛ የሚሰጥ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ
 • ማመልከቻ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ መጠየቂያ ቅፅ 2 ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
  መጠየቂያ ቅፅ 7 እና 8 ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ መጠየቂያ ቅፅ 7 እና 8   
 • የአመልካቹ አገልግሎቱ ቢያንስ 6 ወር የፀና ዜግነት ከተሠጠው አገር የተሰጠ ፓስፖርት ኦርጂናልና አንድ  ኮፒ
 • ወቅታዊ የሆነ የጋብቻ ምስክር ወረቀት (ወደ አማርኛ ወይም ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ የተተረጎመ) እና በ Landgericht ወይም በAmtsgericht ወይም በRegierungspräsidium የተረጋገጠ ኦርጂናል ሰነድና አንድ ኮፒ
 • የተረጋገጠው ወቅታዊ የሆነ የጋብቻ ምስክር ወረቀት በቆንስላ ጽ/ቤትም ይረጋገጣል
 • የአመልካቹ ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፎች (ከጀርባው ሙሉ ስም የተፃፈበት፣ ከበስተኃላው ነጭ የሆነ፣ ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
 • የባለቤት በትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ እና የጀርመን ፓሰፖርት ኦርጂናልና አንድ ኮፒ
 • ወቅታዊ የሆነው የጋብቻ ምስክር ወረቀት ለማረጋገጥ የአገልግሎት ክፍያ 81 €
 • ለመታወቂያው የአገልግሎት ክፍያ የ200 ለመታወቂያው (የአሜሪካን ዶላር) ተመጣጣኙን በቀኑ ምንዛሪ በዩሮ (€) ነው የሚከፈለው
 • የሚገኙበት ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ መፃፍ
 • ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 30 ደቂቃ
 • አዲሱ መታወቂያ ተሰርቶ እስኪመጣ ከሁለት እስከ ሶስት ወር ይቆያል
 • አዲሱ በትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ ከኢሚግሬሽን ተስርቶ ሲመጣ በፖስታ እንዲላክሎት መመለሻ ፖስታ ቴምብር (የ 4,05 €) ለጥፈውና አድራሻዎትን ፅፈው ይላኩልን
10.  የጠፋው የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ለመተካት
 • ማመልከቻ ቅፅ በመሙላት ማቅረብ መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
 • መጥፋቱን ያመለከቱበት ከፖሊስ የተሰጠ ማስረጃ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ ማቅረብ
 • ዜግነት ከወሰዱበት ሀገር የተሰጠና አገልግሎቱ ቢያንስ ስድስት ወር የፀና ፓስፖርት ኦርጂናልና አንድ ኮፒ  ማቅረብ፤
 • አግባብ ባለው አካል የተሰጠና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የልደት ሰርተፊኬት ኦርጂናልና አንድ ኮፒ፤ ወይም
 • የአመልካቹ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርት አንድ ኮፒ፤ ወይም
 • የጠፋው የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ አንድ ኮፒ
 • የጠፋው መታወቂያ ሲያወጡ አሻራ ካልሰጡ በአካል መጥተው አሻራ መስጠት ያስፈልጋል
 • ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፍ ማቅረብ (ከጀርባው ሙሉ ስም የተፃፈበት፣ ከበስተኃላው ነጭ የሆነ፣ ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
 • የሚገኙበት ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ መፃፍ
 • ሰነዶችን በፖስታ የሚልኩት ከሆነ ለአገልግሎት የሚከፈለው በአካውንታችን አስተላልፈውልን የከፈሉበት ማስረጃ (Kontoauszug) አብረው ይላኩልን
 • ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 28 ደቂቃ
 • አዲሱ መታወቂያ ተሰርቶ እስኪመጣ ከሁለት እስከ ሶስት ወር ይቆያል
 • አዲሱ በትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ ከኢሚግሬሽን ተስርቶ ሲመጣ በፖስታ እንዲላክሎት መመለሻ ፖስታ ቴምብር (የ 4,05 €) ለጥፈውና አድራሻዎትን ፅፈው ይላኩልን
11. ውክልና መወከል ወይም ውክልና መሻር ለሚፈልጉ ተገልጋዮች፡-
 1. የውክልና ስልጣን ማስረጃ ወይም መሻሪያ ጽፎ እና ፈርሞ ማቅረብ
 2. ፓስፖርት ፎቶ ያለበት ገፅ ብቻ ሁለት ኮፒ
 3. የመኖርያ ፈቃድ ሁለት ኮፒ
 4. የጀርመን ዜጋ የሆነና በትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ካርድ ያለው፡- የጀርመን ፓስፖርት ፎቶ ያለበት ገፅ ብቻ ሁለት ኮፒ፣ በትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ካርድ ሁለት ኮፒ
 5. የጀርመን ዜጋ የሆነና በትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ካርድ የሌለው፡- የጀርመን ፓስፖርት ፎቶ ያለበት ገፅ ብቻ ሁለት ኮፒ
 6. በጊዜያዊ የጉዞ ሰነድየሚኖሩ ከሆኑ፡- የአመልካቹ የጉዞ ሰነድ (Reiseausweis) ያለበት ገፅ ብቻ ሁለት ኮፒ፣ የመኖርያ ፈቃድ ሁለት ኮፒ
 7. በስደተኛ መታወቂያ የሚኖሩ ከሆኑ፡- የስደተኛ መታወቂያ ሁለት ኮፒ
  • ንብረትን በተመለከተ ለመወከል ከሆነ ወደ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ በአካል መምጣት ግዴታ ነው፤ የውክልና ስልጣን ማስረጃ ፎርም ተሞልቶ ወይም ተጽፎ እና ተፈርሞ ማቅረብ፣ ከላይ በተራ ቁጥር 2-7 ከተጠቀሱት ሰነዶች መካከል እርስዎን የሚመለከት ሰነድ ኦርጂናል እና ሁለት ገጽ ኮፒ ማቅረብ አለብዎት
  • በአካል እዚህ የሚመጡ ከሆነ የአገልግሎቱ ክፍያ የሚከፈለው በካሽ ነው
  • በኢትዮጵያ የወደፊት ንብረት ማፍራት ወይም አዲስ ንብረት ለመግዛት የሚችሉት ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለሆኑ ወይም ትውልድ ኢትዮጵያዊ ለሆኑ ብቻ ነው
  • የወካይ ሙሉ ስም የሚሞላው መታወቂያው/ID ላይ ባለው መሰረት ነው
  • የውክልናው ስልጣኑ ንብረትን የማይመለከት ከሆነና ሌሎች ጉዳዮች ሰነድ እንዲረጋገጥ ከሆነ በአካል መምጣት አይጠበቅቦትም፡፡ /ለምሳሌ የልደት፣ ስም ለውጥ ወዘተ ---/ ሰነዱን አሟልተው በፖስታ መላክ ይችላሉ
  • በፖስታ ለሚልኩ መሟላት ያለባቸው ጉዳዮች፡-
   • የውክልና ስልጣን ማስረጃ ፎርም ተሞልቶ ወይም ተጽፎ እና ተፈርሞ መላክ አለብዎት፤
   • ከላይ በተራ ቁጥር 2-7 ከተጠቀሱት ሰነዶች መካከል እርስዎን የሚመለከት ሰነድ በኮፒ ብቻ መላክ አለብዎት (ኦርጂናል ሰነድ መላክ የለበትም)፤
   • መመለሻ ፖስታ ላይ እርሶ የሚገኙበትን አድራሻ ጽፈው እና ለመመለሻ የሚሆን በቂ ቴምብር (4,05 €) ለጥፈው መላክ አለብዎት፤
   • ለአገልግሎቱ የሚከፈለውን ገንዘብ በጽ/ቤቱ አካውንት ቁጥር(Commerzbank Frankfurt am Main ፣ IBAN:- DE56 5004 00000 582673000 ፣ BIC:- COBADEFFXXX)አስተላልፈው የከፈሉበት ማስረጃ መላክ አለብዎት
 • የልደት ሰርተፍኬት በተመለከተ፡- ሲወክሉ መወከል የሚችሉት ሚስት ወይም ባል ወይም ልጅ ወይም አባት/እናት ወይም እህት/ወንድም ወይም አያት ነው
 • ውክልናው በኤምባሲው ከተረጋገጠ በኋላ እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ማስተካከያ ለማድረግ ከተፈለገና ኦርጅናሉ የተረጋገጠው የውክልና ሰነድ ከቀረበ አዲሱ የውክልና ሰነድ ያለክፍያ ይረጋገጣል
 • የአገልግሎት ክፍያውን ተመን መጨመር ወይም መቀነስ ክልክል ነው
 • የውክልና ስልጣን መስጫ ማስረጃው በሕግ አዋቂዎች ቢፃፍ ወይም ከታች ለናሙና ከተዘጋጁት ብትጠቀሙ ይመረጣል
 • በአካል አሟልተው ከቀረቡ በ20 ደቂቃ ውስጥ ይዘጋጃል፣ በፖስታ ተሟልቶ ከተላከ በ8 ቀን ውስጥ ተሰርቶ ይላካል
 • የአገልግሎት ክፍያ በኢትዮጵያ ፓስፖርት ለሚኖርና የውጭ ዜጋ ሆኖ በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ያለው 55.80 € ሲሆን
 • ለውጪ ዜጎችና በስደተኛ መታወቂያ ወይም በጊዜያዊ የጉዞ ሰነድ የሚኖሩ ከሆነ 85.50 € ነው

ለናሙና የተዘጋጁ የውክልና መስጫ ቅፆች ለማግኘት እዚህ ይጫኑ፡፡

12.  የተለያየ ሰነድ ለማረጋገጥ
 • የሚረጋገጠው ሰነድ በ Notar እና Landgericht ወይም በAmtsgericht ወይም በRegierungspräsidium አረጋግጦ አርጂናል ሰነድና አንድ ኮፒ ከማመልከቻው ጋር  ማቅረብ
 • የሚረጋገጠው ሰነድ የግል ከሆነ የአመልካች ፓስፖርትና የመኖርያ ፈቃድ አንድ ኮፒ
 • የውጭ ዜጋ የሆነና በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ያለው የፓስፖርትና የመታወቂያ አንድ ኮፒ
 • የሚረጋገጠው ሰነድ የድርጅት ከሆነ ድርጅቱ የተመዘገበበት ማስረጃ አንድ ኮፒ
 • የሚገኙበት ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ መፃፍ
 • በአካል እዚህ የሚመጡ ከሆነ የአገልግሎቱ ክፍያ በካሽ ወይም በካርድ ነው የሚከፍሉት
 • ማመልከቻው በፖስታ የሚልኩት ከሆነ ለአገልግሎት የሚከፈለው ገንዘብ በአካውንታችን አስተላልፈውልን የከፈሉበት ማስረጃ (Kontoauszug) አብረው ይላኩልን የሚረጋገጠው አርጂናል ሰነድና ሌላው ሰነድ በኮፒ ይላክሉን ከዚህ በተጨማሪ መመለሻ ፖስታ ቴምብር (የ 4,05 €) ለጥፈውና ኣድራሻዎን ፅፈው ይላክሉን
 • በአካል ከቀረቡ በ 19 ደቂቃ ውስጥ ይዘጋጃል፣ በፖስታ ከተላከ በ8 ቀን ውስጥ ተሰርቶ ይላካል
 • የአገልግሎት ክፍያ በኢትዮጵያ ፓስፖርት ለሚኖርና የውጭ ዜጋ ሆኖ በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ 53,10 € ሲሆን ለውጪ ዜጎችና በስደተኛ መታወቂያ ወይም በጊዜያዊ የጉዞ ሰነድ የሚኖሩ ከሆነ 81 € ነው
13.  የፍቺ ማረጋገጫ ሰነድ ለማረጋገጥ
 • ጥያቄውን በማመልከቻ ማቅረብ
 • ስድስት ወር ያልሞላው አግብተው መፋታቶን የሚገልፅ ሕጋዊ የፍርድ ቤት ማስረጃ አርጂናልና አንድ ኮፒ ወይም
 • ከጀርመን Meldestelle ሙሉ አድራሻና የተፋታ/ች (geschieden) የሚል ወቅታዊ ማስረጃ በNotar እና Landgericht ወይም በAmtsgericht ወይም በRegierungspräsidium አረጋግጦ አርጂናልና አንድ ኮፒ ማቅረብ
 • የአመልካች ፓስፖርትና የመኖርያ ፈቃድ አንድ ኮፒ
 • የውጭ ዜጋ የሆነና በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ያለው የፓስፖርትና የመታወቂያ አንድ ኮፒ
 • የሚገኙበት ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ መፃፍ
 • በአካል እዚህ የሚመጡ ከሆነ የአገልግሎቱ ክፍያ በካሽ ወይም በካርድ ነው የሚከፈለው
 • ማመልከቻው በፖስታ የሚልኩት ከሆነ ለአገልግሎት የሚከፈለው በአካውንታችን አስተላልፈውልን የከፈሉበት ማስረጃ (Kontoauszug) አብረው ይላኩልን የሚረጋገጠው ዋናው ሰነድና ሌላው ሰነድ በኮፒ ይላክሉን ከዚህ በተጨማሪም መመለሻ ፖስታ ቴምብር (የ 4,05 €) ለጥፈውና ኣድራሻዎን ፅፈው ይላክሉን
 • በአካል ከቀረቡ በ 19 ደቂቃ ውስጥ ይዘጋጃል፣ በፖስታ ከተላከ በ8 ቀን ውስጥ ተሰርቶ ይላካል
 • የአገልግሎት ክፍያ በኢትዮጵያ ፓስፖርት ለሚኖርና የውጭ ዜጋ ሆኖ በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ 53,10 € ሲሆን ለውጪ ዜጎችና በስደተኛ መታወቂያ ወይም በጊዜያዊ የጉዞ ሰነድ የሚኖሩ ከሆነ 81 € ነው
14.  ያላገቡ ስለመሆንዎ ማረጋገጫ ደብዳቤ ሲያመለክቱ
 • ጥያቄውን በማመልከቻ ማቅረብ
 • ከጀርመን Meldestelle ሙሉ አድራሻና ያላገባ (ledig) የሚል ወቅታዊ ማስረጃ በNotar እና Landgericht ወይም በAmtsgericht ወይም በRegierungspräsidium አረጋግጦ አርጂናልና አንድ ኮፒ ማቅረብ
 • የአመልካች ፓስፖርትና የመኖርያ ፈቃድ አንድ ኮፒ
 • የውጭ ዜጋ የሆነና በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ያለው የፓስፖርትና የመታወቂያ አንድ ኮፒ
 • የሚገኙበት ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ መፃፍ
 • በአካል እዚህ የሚመጡ ከሆነ የአገልግሎቱ ክፍያ በካሽ ወይም በካርድ ነው የሚከፈለው
 • ማመልከቻው በፖስታ የሚልኩት ከሆነ ለአገልግሎት የሚከፈለው በአካውንታችን አስተላልፈውልን የከፈሉበት ማስረጃ (Kontoauszug) አብረው ይላኩልን የሚረጋገጠው ኦርጂናል ሰነድና ሌላው ሰነድ በኮፒ ይላክሉን ከዚህ በተጨማሪ መመለሻ ፖስታ ቴምብር (የ 4,05 €) ለጥፈውና ኣድራሻዎን ፅፈው ይላክሉን
 • በአካል ከቀረቡ በ 19 ደቂቃ ውስጥ ይዘጋጃል፣ በፖስታ ከተላከ በ8 ቀን ውስጥ ተሰርቶ ይላካል
 • የአገልግሎት ክፍያ በኢትዮጵያ ፓስፖርት ለሚኖርና የውጭ ዜጋ ሆኖ በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ 53,10 € ሲሆን ለውጪ ዜጎችና በስደተኛ መታወቂያ ወይም በጊዜያዊ የጉዞ ሰነድ የሚኖሩ ከሆነ 81 € ነው
15.  በሕይወት እንዳሉ የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ሲያመለክቱ
 • ማመልከቻውን በአካል ቀርበው ማቅረብ
 • የአመልካች ፓስፖርትና የመኖርያ ፈቃድ አንድ ኮፒ
 • ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 17 ደቂቃ
 • አገልግሎቱ በነፃ የሚሰጥ ነው
16. ከወንጀል ነፃ ስለመሆንማረጋገጫ ደብዳቤ ሲያመለክቱ 
 • ማመልከቻውን ከነምክንያቱ ማቅረብ ለሰላማዊ ሰዎች የጣት አሻራ ማንሻ ሰሌዳ
 • ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፎች ማቅረብ (ከጀርባው ሙሉ ስም የተፃፈበት፣ ከበስተኃላው ነጭ የሆነ፣ ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
 • የአመልካች ፓስፖርትና የመኖርያ ፈቃድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ
 • የሚገኙበት ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ መፃፍ
 • የአመልካቹና ሀገር ቤት ጉዳዩን ተከታትሎ የሚያስፈፅም የተወካይ ስም አድራሻና ስልክ ቁጥር ማመልከቻው ላይ መግለፅ
 • በአካል መምጣትና አሻራ መስጠት
 • ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 40 ደቂቃ
 • አገልግሎቱ በነፃ የሚሰጥ ነው
17. ጠቅልለው ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ታክስ/ቀረጥ ሳይከፍሉና ከፍለው እቃዎች ለማስገባት

ማንኛውም መንገደኛ፣ ተመላሽ ኢትዮዽያዊ፣ ከስደተኛ ተመላሽ እና በተለያዩ ሙያዎች ኢትዮዽያ ውስጥ ለማገልገል በህጋዊ መንገድ ተቀጥሮ ወይም በሌላ ህጋዊ ስምምነት ኢትዮዽያ ውስጥ ለማገልገል በአየር ወይም በየብስ ወደ ኢትዮዽያ የሚገባ ወይም ከኢትዮዽያ የሚወጣ ኢትዮዽያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮዽያዊ ወይም የውጭ አገር ዜጋ መንግስት በሚያደርገው ልዩ ጥሪ መሰረት የሚመጣ ኢትዮዽያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮዽያዊ ወይም የውጭ ዜጋ ማንኛውም ባለሀብት እንዲሁም አንድ ዓመት እና ከዚያ በላይ በግል ስራ በቅጥር ወይም በትምህርት ውጭ አገር የቆየ ኢትዮዽያዊ ወደ አገር ውስጥ በሚያስገቡዋቸው ወይም ከአገር በሚያስወጡዋቸው የግል መገልገያ ዕቃዎች እና ለንግድ የማይውሉ የግል መገልገያ ዕቃዎች መረጃ ለማግኘት ከዚህ የተያያዙትን ይጫኑ:-
1. መረጃ
2. መረጃ
3. መረጃ

ማመልከቻዎትን በቆንስላ ጽ/ቤት ፍራንክፈርት ሲያቀርቡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለቦት

 • ከቀረጥ ነፃ ደብዳቤ እንድንፅፍሎት በማመልከቻ ይጠይቁ᎓ መጠየቀያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
 • ወደሚኖሩበት ሲመጡ የተመዘገቡበት መረጃ (Anmeldebestätigung)
 • አሁን ያሉበትን ለመመለሶ ማረጋገጫ ደብዳቤ (Abmeldebestätigung)
 • ዜግነትዎ ኢትዮጵያዊ ከሆነ የፓስፖርትና የጀርመን መኖሪያ ፈቃድ ኦርጂናልና ሁለት ኮፒ
 • ዜግነትዎ ጀርመን ከሆነ የፓስፖርትና በትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ኦሪጅናልነ ሀለት ኮፒ
 • ከስደት ተመላሽ (ባሉበት አገር ተቀባይነት ያላገኙ) ከሆኑ የመታወቂያ ኦሪጅናልና ሀለት ኮፒ
 • ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፎች ማቅረብ (ከጀርባው ሙሉ ስም የተፃፈበት፣ ከበስተኃላው ነጭ የሆነ፣ ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
 • የሚገኙበት ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ መፃፍ
 • በፖስታ የሚልኩት ከሆነ ከላይ የተጠቀሱትና መመለሻ ፖስታ (የ 4,05 €) ቴምብር ለጥፈውና አድራሻዎትን ፅፈው ይላኩ
18. ለ TIN-Number የሚወሰድ አሻራ
 • ማመልከቻ መፃፍ
 • የሚገኙበት ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ መፃፍ
 • የኢትዮዽያ ፓስፖርት ፎቶ ያለበት ገፅና የጀርመን አገር መኖርያ ፈቃድ አሪጂናልና ሁለት ኮፒ
 • ዜግነትዎ ጀርመን ከሆነ ዜግነት ከተሰጠው አገር የተሰጠ ፓስፖርት ፎቶ ያለበት ገፅና በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ኦሪጂናልና ሁለት ኮፒ
 • ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፎች ማቅረብ (ከጀርባው ሙሉ ስም የተፃፈበት፣ ከበስተኃላው ነጭ የሆነ፣ ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
 • በአካል መምጣትና አሻራ መስጠት
 • ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 20 ደቂቃ
 • አገልግሎቱ በነፃ የሚሰጥ ነው
19. በጀርመን ሕይወቱ ያለፈ ዜጋን አስከሬን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ
 • የሟች ፓስፖርት ኮፒ የስደተኛ መታወቅያ ኮፒ ወይም የጉዞ ሠነድ Reiseausweis ኮፒ
 • ሕይወታቸውን ማለፉን የሚያረጋግጥ ማስረጃ (Todesbescheinigung)
 • የአስከሬን ፓስፖርት (Leichenpass)
 • ለሟች የሚሰጥ ሠርተፊኬት (Sterbeurkunde)
 • የአስከሬኑ ጉዳይ ከሚያስፈፅም ድርጅት (Bestattungsinstitut) የሚመጣ መረጃ (Bescheinigung) Zertifikat des Bestattungsinstituts.
 • አስከሬኑ ይዞ የሚሄድ ሰው ካለ በማመልከቻው ለአስከሬኑ ሙሉ ሃላፊነት እንደሚወስድ ፅፎ የሚኖርበትን አድራሻና ስልክ ቁጥር ከፃፈ በኃላ ፈርሞበት የፓስፖርትና የመኖርያ ፈቃድ ኮፒ አብሮ ይልካል
  ከአስከሬኑ አብሮ የሚሄድ ሰው ከሌለ የአስከሬኑ ተቀባይ ነዋሪነቱ ኢትዮጵያ ከሆነ በማመልከቻው ሙሉ ሃላፊነት እንደሚወስድ በመፃፍ የፓስፖርት ኮፒ ወይም የቀበሌ መታወቂያ ኮፒ ከነሙሉ አድራሻ ጋር (ከተማ ክፍለከተማ ወረዳ ቀበሌ የቤት ቁጥር) እና የስልክ ቁጥሩን በመፃፍ ኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ማመልከት ይኖርበታል
 • የትኬት ኮፒ
 • ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 24 ደቂቃ
20. የተለያየ የማረጋገጫ ደብዳቤ ሲያመለክቱ
 • ማመልከቻ መፃፍ
 • የጊዜያዊ መኖርያ ፍቃድ አንድ ኮፒ ወይም
 • የአመልካች ፓስፖርትና የጀርመን መኖርያ ፈቃድ አንድ ኮፒ
 • የሚገኙበት ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ መፃፍ
 • በአካል መቅረብ ወይም በፖስታ መላክ:: በፖስታ ሲልኩ መመለሻ ፖስታ ቴምብር (የ 4,05 €) ለጥፈውና አድራሻዎትን ፅፈው ይላኩ
 • በአካል ከቀረቡ በ 17 ደቂቃ ውስጥ ይዘጋጃል፣ በፖስታ ከተላከ በ8 ቀን ውስጥ ይላካል

21. የዜግነት መልቀቂያ ደብዳቤ ሲያመለክቱ

 • ማመልከቻ መፃፍ
 • የአመልካች የኢትዮጵያ ኦርጅናል ፓስፖርትና የጀርመን መኖርያ ፈቃድ አንድ ኮፒ ማቅረብ
 • ከጀርመን ሀገር የሚሰጥ ደብዳቤ (Einbürgerungszusicherung) ኦርጅናሉን ማቅረብ
 • የሚገኙበት ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ መፃፍ
 • በአካል መቅረብ ወይም በፖስታ መላክ:: በፖስታ ሲልኩ መመለሻ ፖስታ ቴምብር (የ 4,05 €) ለጥፈውና አድራሻዎትን ፅፈው ይላኩ
 • በአካል ከቀረቡ በ 17 ደቂቃ ውስጥ ይዘጋጃል፣ በፖስታ ከተላከ በ8 ቀን ውስጥ ይላካል
22. በቆንስላ ጽ/ቤት ጋብቻ ለመፈፀም የወጣ ዝርዝር መረጃ ሙሉ ይዘት ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ገንዘብ የሚያስተላልፉበት የባንክ አካውንት ቁጥር

Commerzbank Frankfurt am Main

IBAN:- DE56 5004 00000 582673000

BIC:- COBADEFFXXX

ማሳሰቢያ

 • በአካል እዚህ የሚመጡ ከሆነ የአገልግሎቱ ክፍያ በካሽ ወይም በካርድ መክፈል ይችላሉ
 • ማመልከቻዎትን በፖስታ የሚልኩት ከሆነ ለአገልግሎት የሚከፈለው ገንዘብ በካሽ መላክ በጥብቅ የተከለከለ ነው
 • ደረሰኝ ተቆርጦ ገቢ የተደረገ ክፍያ አይመለስም
 • በባንክ ቁጥራችን ለአገልግሎት ያስተላለፉት ክፍያ አገልግሎት ሳያገኙ ቢቀርና ስድስት ወር ካለፈው ተመላሽ አይሆንም
 • ማመልከቻውን በፖስታ የሚልኩት ከሆነ መመለሻ ፖስታ ቴምብር (በአደራ መላኪያ የሚሆን)ለጥፈውና  አድራሻዎትን ፅፈው ይላኩ
 • ጀርመን አገር በኢትየጵያ ፓስፖርት የሚኖሩ ከሆነ ወደ ኢትየጵያ ሲሄዱ ቪዛ አያስፈልጎትም:: ወደ ኢትዮጵያ በሚሄዱበት ጊዜ ግን ፓስፖርቱ ቢየንስ የስድስት ወር አገልግሎት ያለው መሆን አለበት
 • የሚያስፈፅሙት ጉዳይ ካለ ብቻ ወደ ቆንስላ ጽ/ቤት እንዲመጡ በትህትና እየገለፅን ስለተረዱን በቅድሚያ እናመሰግናለን