የቡና ማስተዋወቂያ ዌብናር በፓሪስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዘጋጅነት ተካሄደ

የቡና ማስተዋወቂያ ዌብናር በፓሪስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዘጋጅነት ተካሄደ
=======================
በፈረንሳይ ፓሪስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ጥር 03 ቀን 2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቡና ማስተዋወቂያ ፎረምን በበይነ መረብ አካሂዷል ፡፡
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ዘርፍ ሚኒስትር የዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ፅዮን ተክሉ በፎረሙ ላይ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።
ክብርት ሚኒስትር ዴኤታ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢትዮጵያ የአረቢካ ቡናን ለሰው ልጆች ያበረከተች ታሪካዊት ሀገር፣ የሰው ዜር መገኛ በመሆንዋ፣ “ምድረ ቀደምት!” የሚል መጠሪያ በትክክል የሚገልፃት እና በዚሁ ብራንድ ስም በመጠቀም ፀጋዎቹን ለዓለም በማስተዋወቅ ላይ መሆንዋን ገልፀዋል።
በማስከተል የኢትዮጵያ ባለልዩ ጣዕም ቡና ዋና ዋና ባህሪያትን፣ የቡና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎችን፣ ከገበያ አንፃር የኢትዮጵያ ቡና መዳረሻችን በዝርዝር ያብራሩት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ በመጨረሻም የኢትዮጵያ መንግስት እና የኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ የቡና ንግድን ለማሳደግ የተቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ለተሳታፊዎቹ አረጋግጠዋል ፡፡
በፈረንሳይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አማባሳደር አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ በበከኩላቸው፣ አብዛኛው የቡና ንግድ ሥራ የሚካሄደው በደላሎች አማካይነት መሆኑ ጠቁመው፣ የቡና ንግዱ በቀጥታ በኤክስፖርቶችና አስመጪዎች መካከል የሚካሄድባቸውን መንገዶች መፈተሽ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል ፡፡
አምባሳደሩ በመዳረሻ ገበያዎች የኢትዮጵያን ቡና የማስተዋወቅ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በማመልከት፣ በቡና ንግድን ዘርፍ ተሳታፊ ለሆኑት አካላት የተጠናከረ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል ፡፡
በስብሰባው በቡና ኤክስፖርት ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች፣ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር፣ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎችን ከኢትዮጵያ ወገን፣ እንዲሁም፤ የቡና አስመጪዎች እና Roasters ከፈረንሣይ፣ ስፔን እና ፖርቱጋል፣ የተሳተፉ ሲሆን፣ ባጠቃላይ ከ53 በላይ የቡና ዘርፍ ቁልፍ ተዋንያን በፎረሙ ላይ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡
በፎረሙ ላይ በኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ተወካዮች ፣ በኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበራት እና በቡና ኤክስፖርት የተሰማሩ ኩባንያዎች ስለ ቡና ዘርፍና ስለ ቡና ቢዝነስ ገለፃ ተደርጓል፡፡
Posted in News.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *