አዲስ ወይም ቅያሪ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ

 • ማመልከቻ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
 • የአመልካቹ አገልግሎቱ ቢያንስ 6 ወር የፀና ዜግነት ከተሠጠው አገር የተሰጠ ፓስፖርት ዋናውና አንድ  ኮፒ
 • በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ከነበርዎት ያለቀው በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ዋናውና አንድ ኮፒ
 • የአመልካቹ ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፎች (ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
 • አግባብ ባለው አካል የተሰጠና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የልደት ሰርተፊኬት ዋናውና አንድ ኮፒ፤ ወይም
 • የአመልካቹ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርት አንድ ኮፒ፤ ወይም
 • ከፍርድቤት የተሰጠ ሆኖ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የወላጅ የወራሽነት ማስረጃ አንድ  ኮፒ ወይም
 • ስልጣን ካለው ፍርድ ቤት የተሰጠና በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ  የኢትዮጵያዊ ልጅ የነበረ መሆኑና ለጉዲፈቻነት የተሰጠ እንደነበረ የሚያሳይ የወላጆች ማስረጃ ዋናውና አንድ ኮፒ ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ ከሆነ በራሱ ጠያቂነት፣ ዕድሜው ከ18 በታች ከሆነም በአሳዳጊዎቹ ጠያቂነት፤ ወይም
 • ወላጆቹ ኢትዮጵያዊ ሆነው ስልጣን ካለው ፍርድ ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል ተረጋግጦ የቀረበ የአባትነት ወይም የእናትነት ማረጋገጫ፤ ወይም
 • የኢትዮጵያ ተወላጅነቱን በተጨባጭ ማስረጃ አባቱ ፣ እናቱ ፣ አያቱ፣ ወይም ቅድም አያቱ ቢያንስ በአንዱ የኢትዮጵያ ዜግነት ይዞ የነበረ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማስረጃ
 • ለመታወቂያው የአገልግሎት ክፍያ የ200$ (የአሜሪካን ዶላር) ተመጣጣኙን በቀኑ ምንዛሪ በዩሮ (€) ነው የሚከፈለው
 • ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 30 ደቂቃ
 • አዲሱ መታወቂያ ተሰርቶ እስኪመጣ ከሁለት እስከ ሶስት ወር ይቆያል

አካለ መጠን ላልደረሱ የኢትዮጵያዊ ተወላጅ ልጆች በትውልድ ኢትዮጵያዊ  የውጭ ዜጋ መታወቂያ

 • ማመልከቻ ቅፅ መሙላት መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
 • የልጁ አገልግሎቱ ቢያንስ ስድስት ወር የፀና ዜግነት ከተሠጠው አገር የተሰጠ ፓስፖርት ዋናውና አንድ  ኮፒ
 • የልጁ ሕጋዊ የልደት ምስክር ወረቀት (ወደ እንግሊዝ ቋንቋ የተተረጎመ)  እና በ Landgericht ወይም በ Regierungspräsidium ወይም በ Amtsgericht የተረጋገጠ ዋናውና አንድ  ኮፒ
 • የተረጋገጠው የልደት ሰረቲፊኬት በቆንስላ ጽ/ቤትም ይረጋገጣል
 • የልጁ  ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፎች ማቅረብ (ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
 • የወላጅ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ እና የጀርመን ፓሰፖርት ወይም የኢትዮጵያ ፓስፖርት አንድ ኮፒ
 • የልደት ሰርቲፊኬቱን ለማረጋገጥ የአገልግሎት ክፍያ 76,50 € ሲሆን
 • ለመታወቂያው የአገልግሎት ክፍያ የ20$ (የአሜሪካን ዶላር) ተመጣጣኙን በቀኑ ምንዛሪ በዩሮ (€) ነው የሚከፈለው
 • ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 30 ደቂቃ
 • አዲሱ መታወቂያ ተሰርቶ እስኪመጣ ከሁለት እስከ ሶስት ወር ይቆያል

  የጠፋው የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ለመተካት

 • ማመልከቻ ቅፅ በመሙላት ማቅረብ መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
 • መጥፋቱን ያመለከቱበት ከፖሊስ የተሰጠ ማስረጃ ዋናውና አንድ ኮፒ ማቅረብ
 • ዜግነት ከወሰዱበት ሀገር የተሰጠና አገልግሎቱ ቢያንስ ስድስት ወር የፀና ፓስፖርት ዋናውና አንድ ኮፒ  ማቅረብ፤
 • አግባብ ባለው አካል የተሰጠና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የልደት ሰርተፊኬት ዋናውና አንድ ኮፒ፤ ወይም
 • የአመልካቹ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርት አንድ ኮፒ፤ ወይም
 • የጠፋው የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ አንድ ኮፒ
 • የጠፋው መታወቂያ ሲያወጡ አሻራ ካልሰጡ በአካል መጥተው አሻራ መስጠት ያስፈልጋል
 • ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፍ ማቅረብ (ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
 • ለመጀመርያ ጊዜ በጠፋ ፓስፖርት ምትክ በመደበኛ ክፍያ ተጨማሪ 20%
 • ለሁለተኛ ጊዜ በጠፋ ፓስፖርት ምትክ በመደበኛ ክፍያ ተጨማሪ 50%
 • ለሶስተኛ ጊዜ በጠፋ ፓስፖርት ምትክ በአምስት ዓመት ውስጥ ጥያቄ ካቀረበ በመደበኛ ክፍያ ተጨማሪ 100%
 • መታወቂያው ተበላሽቶ ሲቀየር በመደበኛ ክፍያ ላይ ተጨማሪ 10%
 • ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 30 ደቂቃ
 • አዲሱ መታወቂያ ተሰርቶ እስኪመጣ ከሁለት እስከ ሶስት ወር ይቆያል