የኢትዮጵያና ጀርመን የኢነርጂ አጋርነት የፈጠራ ውድድር ፕሮግራም ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያና ጀርመን የኢነርጂ አጋርነት የፈጠራ ውድድር ፕሮግራም ይፋ ሆነ
ነሐሴ 26 ቀን 2012 ዓ.ም ፤አዲስ አበባ፤ በኢትዮጵያ-ጀርመን የኢነርጂ አጋርነት ፕሮግራም በኢነርጂ ዘርፍ የፈጠራ ውድድር ይፋ ሆነ፡፡የፈጠራ ውድድሩ ይፋ የሆነው ከ90 በላይ የኢትዮጵያና የጀርመን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች፣ የግል ዘርፍ ተሳታፊዎችና የፈጠራ ዘርፍ ያሉ ባለሙያዎች በተሳተፉበት በበይነ መረብ በተካሄደ ሁነት ነው፡፡
‹‹Decentralize Energy Solution ያልተማከለ የኢነርጂ መፍትሔ›› በሚል መሪ ቃል በበይነ መረብ በተካሄደው በዚህ ፕሮግራም የፈጠራ ውድድሩ ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች፣ ተመራማሪዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎች ይፋ ሆኗል፡፡ ውድድሩ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይልን ተደራሽነት ለማስፋትና ለገጠሩም ነዋሪዎች ጭምር ለማድረስ የምታደርገውን ጥረት የሚያግዝ ሲሆን የሚቀርበው የፈጠራ ሥራ ከአካባቢ ብክለት የፀዳ፣ አስተማማኝ ፣ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብ እንዲሁም አስፈላጊ ለሆኑ ዘርፎች ለጤና፣ለውሃ፣የኮቪድ ስርጭትን ለመከላከል የሚያግዝና በዘላቂነት ሊያገለግል የሚችል ዓይነት መሆን እንደሚኖርበት ተጠቁሟል፡፡
የኢትዮጵያና ጀርመን የኢነርጂ አጋርነትና ትብብር እ.አ.አ ከሕዳር 2019 በኢትዮጵያ ውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለና በጀርመን የኢኮኖሚ ጉዳዮችና ኢነርጂ ሚኒስትር ፒተር አልትሜየር (Peter Altmaier) አማካኝነት ተፈርሞ የተጀመረ የትብብር ስምምነት ነው፡፡
ውድድሩን በሚመለከት ዝርዝር መረጃ ከ‹‹ Website of the Ethiopian-German Energy Partnership›› ማግኘት ይቻላል፡፡
130
People Reached
3
Engagements
Boost Unavailable
2
Posted in News.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *