የውክልና አገልግሎት

   ውክልና መወከል ወይም ውክልና መሻር ለሚፈልጉ ተገልጋች:-

 1. የውክልና ስልጣን ማስረጃ ወይም መሻሪያ ጽፎ እና ፈርሞ ማቅረብ
 2. ፓስፖርት ፎቶ ያለበት ገፅ ብቻ ሁለት ኮፒ
 3. የመኖርያ ፈቃድ ሁለት ኮፒ
 4. የጀርመን ዜጋ የሆነና በትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ካርድ ያለው፡- የጀርመን ፓስፖርት ፎቶ ያለበት ገፅ ብቻ ሁለት ኮፒ፣ በትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ካርድ ሁለት ኮፒ
 5. የጀርመን ዜጋ የሆነና በትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ካርድ የሌለው፡- የጀርመን ፓስፖርት ፎቶ ያለበት ገፅ ብቻ ሁለት ኮፒ
 6. በጊዜያዊ የጉዞ ሰነድየሚኖሩ ከሆኑ፡- የአመልካቹ የጉዞ ሰነድ (Reiseausweis) ያለበት ገፅ ብቻ ሁለት ኮፒ፣ የመኖርያ ፈቃድ ሁለት ኮፒ
 7. በስደተኛ መታወቂያ የሚኖሩ ከሆኑ፡- የስደተኛ መታወቂያ ሁለት ኮፒ
  • ንብረትን በተመለከተ ለመወከል ከሆነ ወደ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ በአካል መምጣት ግዴታ ነው፤ የውክልና ስልጣን ማስረጃ ፎርም ተሞልቶ ወይም ተጽፎ እና ተፈርሞ ማቅረብ፣ ከላይ በተራ ቁጥር 2-7 ከተጠቀሱት ሰነዶች መካከል እርስዎን የሚመለከት ሰነድ ኦርጂናል እና ሁለት ገጽ ኮፒ ማቅረብ አለብዎት
  • በአካል እዚህ የሚመጡ ከሆነ የአገልግሎቱ ክፍያ የሚከፈለው በካሽ ነው
  • በኢትዮጵያ የወደፊት ንብረት ማፍራት ወይም አዲስ ንብረት ለመግዛት የሚችሉት ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለሆኑ ወይም ትውልድ ኢትዮጵያዊ ለሆኑ ብቻ ነው
  • የወካይ ሙሉ ስም የሚሞላው መታወቂያው/ID ላይ ባለው መሰረት ነው
  • የውክልናው ስልጣኑ ንብረትን የማይመለከት ከሆነና ሌሎች ጉዳዮች ሰነድ እንዲረጋገጥ ከሆነ በአካል መምጣት አይጠበቅቦትም፡፡ /ለምሳሌ የልደት፣ ስም ለውጥ ወዘተ —/ ሰነዱን አሟልተው በፖስታ መላክ ይችላሉ
  • በፖስታ ለሚልኩ መሟላት ያለባቸው ጉዳዮች፡-
   • የውክልና ስልጣን ማስረጃ ፎርም ተሞልቶ ወይም ተጽፎ እና ተፈርሞ መላክ አለብዎት፤
   • ከላይ በተራ ቁጥር 2-7 ከተጠቀሱት ሰነዶች መካከል እርስዎን የሚመለከት ሰነድ በኮፒ ብቻ መላክ አለብዎት (ኦርጂናል ሰነድ መላክ የለበትም)፤
   • መመለሻ ፖስታ ላይ እርሶ የሚገኙበትን አድራሻ ጽፈው እና ለመመለሻ የሚሆን በቂ ቴምብር (4,05 €) ለጥፈው መላክ አለብዎት፤
   • ለአገልግሎቱ የሚከፈለውን ገንዘብ በጽ/ቤቱ አካውንት ቁጥር(Commerzbank Frankfurt am Main ፣ IBAN:- DE56 5004 00000 582673000 ፣ BIC:- COBADEFFXXX)አስተላልፈው የከፈሉበት ማስረጃ መላክ አለብዎት
 • የልደት ሰርተፍኬት በተመለከተ፡- ሲወክሉ መወከል የሚችሉት ሚስት ወይም ባል ወይም ልጅ ወይም አባት/እናት ወይም እህት/ወንድም ወይም አያት ነው
 • ውክልናው በኤምባሲው ከተረጋገጠ በኋላ እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ማስተካከያ ለማድረግ ከተፈለገና ኦርጅናሉ የተረጋገጠው የውክልና ሰነድ ከቀረበ አዲሱ የውክልና ሰነድ ያለክፍያ ይረጋገጣል
 • የአገልግሎት ክፍያውን ተመን መጨመር ወይም መቀነስ ክልክል ነው
 • የውክልና ስልጣን መስጫ ማስረጃው በሕግ አዋቂዎች ቢፃፍ ወይም ከታች ለናሙና ከተዘጋጁት ብትጠቀሙ ይመረጣል
 • በአካል አሟልተው ከቀረቡ በ20 ደቂቃ ውስጥ ይዘጋጃል፣ በፖስታ ተሟልቶ ከተላከ በ8 ቀን ውስጥ ተሰርቶ ይላካል
 • የአገልግሎት ክፍያ በኢትዮጵያ ፓስፖርት ለሚኖርና የውጭ ዜጋ ሆኖ በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ያለው 55.80 € ሲሆን
 • ለውጪ ዜጎችና በስደተኛ መታወቂያ ወይም በጊዜያዊ የጉዞ ሰነድ የሚኖሩ ከሆነ 85.50 € ነው

ለናሙና የተዘጋጁ የውክልና መስጫ ቅፆች ለማግኘት እዚህ ይጫኑ፡፡

ለምንሰጠው አገልግሎት ዝርዝር መረጃ ለማግኝት እዚህ ይጫኑ።