1. አዲስ ፓስፖርት ለመጠየቅ
- የፓስፖርት መጠየቂያ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
- ከዚህ በፊት አሻራ ካልሰጡ በቆንስላ ፅ/ቤት በመገኘት አሻራ መስጠት
የአሻራ መውሰጃ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ - ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፎች ማቅረብ (ከጀርባው ነጭ የሆነና ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
- ከኢትዮጵያ ሲወጡ የነበረው የኢትዮጵያ የቀድሞው ፓስፖርት አንድ ኮፒ ማቅረብ
- የቀድሞው ፓስፖርት ኮፒ ከሌለ በሰነድ አልባ አመልክቶ ኢትዮጵያዊነት መጣራት አለበት
- ከሚኖሩበት ሀገር የተሰጠ መኖርያ ፈቃድና የጉዞ ሰነድ አንድ ኮፒ ወይም ከሚኖሩበት ሀገር የተሰጠ ጊዜያዊ መታወቂያ አንድ ኮፒ
- የስም ወይም የዕድሜ ለውጥ ካለ ከሚመለከተው ክፍል የተዘጋጀና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ማስረጃ አርጂናልና አንድ ኮፒ
- አሻራ ካልሰጡ በአካል መገኘት ያስፈልጋል
- ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 26 ደቂቃ
- የአገልግሎት ክፍያ 54 €
- አዲሱ ፓስፖርት ተሰርቶ እስኪመጣ ከሁለት እስከ ሶስት ወር ይቆያል
- አዲሱ ፓስፖርት ከኢሚግሬሽን ተስርቶ ሲመጣ በፖስታ እንዲላክሎት መመለሻ ፖስታ ቴምብር (በአደራ መላኪያ የሚሆን) ለጥፈውና አድራሻዎትን ፅፈው ይላኩልን
2. ፓስፖርት ለማስቀየር
- የፓስፖርት መጠየቂያ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
- አገልግሎቱ ያበቃ ፓስፖርት ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ማቅረብ
- የጀርመን መኖሪያ ፈቃድ አንድ ኮፒ ማቅረብ
- ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፎች ማቅረብ (ከጀርባው ነጭ የሆነና ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
- ያለቀውን ፓስፖርት ሲያወጡ አሻራ ሰጥተው ከነበረ ሰነዶችን በፖስታ መላክ ይችላሉ በፖስታ ሲልኩ ፓስፖርት ኦርጂናልና የጀርመን መኖሪያ ፈቃድ አንድ ኮፒ ይላኩልን
- አገልግሎቱ ያበቃው ፓስፖርት ሲወስዱ 14 ዓመት በታች ከነበሩ የግድ በአካል መምጣት ያስፈልጋል
- የአገልግሎት ክፍያ 54 €
- የስም ለውጥ ካለ ስም የለወጡብት ማስረጃ ማቅረብ
- የስም ለውጥ ማስረጃው ከኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መረጋገጥ አለበት
- የስም ለውጥ ማስረጃው ከጀርመን ከሆነ (ወደ አማርኛ ወይም ወደ እንግሊዝ ቋንቋ የተተረጎመ) እና በ Landgericht የተረጋገጠ አርጂናልና አንድ ኮፒ
- የጀርመን አገር የስም ለውጥ ማስረጃ በቆንስላ ጽ/ቤት መረጋገጥ አለበት
- ለስም ለውጥ ማስረጃ በቆንስላ ጽ/ቤት ለማረጋገጥ የአገልግሎት ክፍያ 53,10 € ነው
- ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 26 ደቂቃ
- አዲሱ ፓስፖርት ተሰርቶ እስኪመጣ ከሁለት እስከ ሶስት ወር ይቆያል
- አዲሱ ፓስፖርት ከኢሚግሬሽን ተስርቶ ሲመጣ በፖስታ እንዲላክሎት መመለሻ ፖስታ ቴምብር (በአደራ መላኪያ የሚሆን) ለጥፈውና አድራሻዎትን ፅፈው ይላኩልን
3. በጠፋ ፓስፖርት ምትክ አዲስ ፓስፖርት ለመጠየቅ
- የፓስፖርት መጠየቂያ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
- ስለመጥፋቱ የፖሊስ ማስረጃ
- የጠፋው ፓስፖርት አንድ ኮፒ ማቅረብ
- የጀርመን መኖሪያ ፈቃድ አንድ ኮፒ
- ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፎች ማቅረብ (ከጀርባው ነጭ የሆነና ሁለቱም ጆሮ ሙሉ በሙሉ የሚታይ መሆን አለበት)
- ለመጀመርያ ጊዜ በጠፋ ፓስፖርት ምትክ በመደበኛ ክፍያ ተጨማሪ 50% የአገልግሎት ክፍያ 81 €
- ለሁለተኛ ጊዜ በጠፋ ፓስፖርት ምትክ በመደበኛ ክፍያ ተጨማሪ 100% የአገልግሎት ክፍያ 108 €
- ለሶስተኛ ጊዜ በጠፋ ፓስፖርት ምትክ በአምስት ዓመት ውስጥ ጥያቄ ካቀረበ በመደበኛ ክፍያ ተጨማሪ 200% የአገልግሎት ክፍያ 162 €
- ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 26 ደቂቃ
- አዲሱ ፓስፖርት ተሰርቶ እስኪመጣ ከሁለት እስከ ሶስት ወር ይቆያል
- አዲሱ ፓስፖርት ከኢሚግሬሽን ተስርቶ ሲመጣ በፖስታ እንዲላክሎት መመለሻ ፖስታ ቴምብር (በአደራ መላኪያ የሚሆን) ለጥፈውና አድራሻዎትን ፅፈው ይላኩልን
4. አዲስ ፓስፖርት ለህጻን
- የፓስፖርት መጠየቂያ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ
- ህፃኑ / ህፃኗ ፓስፖርት እንዲሰጠው እንዲሰጣት የአባትና የእናት ስምምነት ያለበት ማመልከቻ ማቅረብ
- የህፃኑ/የህፃኗ ሕጋዊ የልደት ምስክር ወረቀት (ወደ አማርኛ ወይም ወደ እንግሊዝ ቋንቋ የተተረጎመ) እና በ Landgericht የተረጋገጠ አርጂናልና አንድ ኮፒ
- የተረጋገጠው የልደት ሰረቲፊኬት በቆንስላ ጽ/ቤትም ይረጋገጣል
- የህፃኑ /የህፃኗ ሁለት የቅርብ ጊዜ ባዮሜትሪክ ፎቶግራፎች ማቅረብ
- ህፃኑ /ህፃኗ የሌላ ሀገር ዜግነት የሌለው / የሌላት መሆኑ / መሆኗ የሚያረጋግጥ ሰነድ አርጂናልና አንድ ኮፒ
- የወላጆች ፓስፖርትና የጀርመን መኖሪድ ፈቃድ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ
- ለመስተንግዶ የሚወስደው ጊዜ 26 ደቂቃ
- ለአገልግሎት የሚከፈል ክፍያ ደውልን እናሳውቆታልን
- አዲሱ ፓስፖርት ተሰርቶ እስኪመጣ ከሁለት እስከ ሶስት ወር ይቆያል
- አዲሱ ፓስፖርት ከኢሚግሬሽን ተስርቶ ሲመጣ በፖስታ እንዲላክሎት መመለሻ ፖስታ ቴምብር (በአደራ መላኪያ የሚሆን) ለጥፈውና አድራሻዎትን ፅፈው ይላኩልን