ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ጄ ብሊንከን ጋር ተወያዩ

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ጄ ብሊንከን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ጄ ብሊንከን ጋር ተወያዩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በትግራይ ስላለው ሁኔታ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ጄ ብሊንከን በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት እና ግንኙነቷን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልፀዋል፡፡
በትግራይ ክልል የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ እና የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነት ላይም ተወያይተዋል፡፡
አሜሪካ አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Posted in News.

Leave a Reply