አሜሪካ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሂደት እና ሀገራዊውን ምርጫ ትደግፋለች – የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
አዲስ አበባ ፣ ጥር 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሂደት እና ቀጣዩን ምርጫ እንደምትደግፍ አስታወቁ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው ወቅትም የኢትዮጵያ እና አሜሪካን የሁለትዮሽ ግንኙነት ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ አጽንኦት ሰጥተው መክረዋል፡፡
ሚኒስትሩ በውይይታቸው በትግራይ ክልል ስላለው ቀውስ ስጋታቸውን ገልጸው፥ በቀጣይ የሰው ህይወት እንዳይጠፋ አስተማማኝ እና ያልተገደበ ሰብአዊ ድጋፍ መደረግ እንዳለበት አንስተዋል፡፡
አያይዘውም ሃገራቸው በኢትዮጵያ የለውጥ ሂደቱን እና ቀጣዩን ምርጭ ትደግፋለች ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም አሜሪካ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሁሉን አቀፍ ለውጥ ለመደገፍ ላሳየችው ተነሳሽነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዴሞክራሲያዊ፣ የበለጸገች እና ሰላም የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚደረገው ጥረት በተጠናከረ የአሜሪካ እና ኢትዮጵያ ግንኙነት የተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚደርስም በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አስታውቀዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
30
People Reached
2
Engagements
Boost Unavailable
1